Psalms 110

መሲሑ ንጉሥና ካህን

የዳዊት መዝሙር።

1 እግዚአብሔር ጌታዬን፣
“ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ፣
እስከማደርግልህ ድረስ፣
በቀኜ ተቀመጥ” አለው።

2 እግዚአብሔር ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰድዳል፤
አንተም በጠላቶችህ መካከል ሆነህ ትገዛለህ።
3ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣
ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤
ከንጋት ማሕፀን፣
በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣
የጕልማሳነትህን ልምላሜ
ወይም ጐልማሶችህ እንደ ንጋት ወዳንተ ይመጣሉ ማለት ነው።
እንደ ጠል ትቀበላለህ።

4“እንደ መልከጼዴቅ ሥርዐት፤
አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣
እግዚአብሔር ምሏል፤
እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም።

5ጌታ በቀኝህ ነው፤
በቍጣውም ቀን ነገሥታትን ያደቅቃቸዋል።
6በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤
በየአገሩ ያሉትንም ራሶች ከስክሶ ሬሳ በሬሳ ያደርጋቸዋል።
7መንገድ
ወይም ሥልጣን ለመስጠት ኀይል ያለው ሥልጣን ላይ ያስቀምጠዋል
ዳር ካለች ፈሳሽ ውሃ ይጠጣል፤
ስለዚህ ራሱን ቀና ያደርጋል።
Copyright information for AmhNASV